የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣የግብርና ሚኒስቴር እና የትምህርት ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ አደረጉ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ተከትሎ በቀረበው ጥሪ መሰረት በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል ተብሏል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ደግሞ 1ሺህ ኩንታል ስንዴ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የትምህርት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ለሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የምገባ መርሃ ግብር የሚያግዝ ዘመናዊ ኢንዱስትሪያል ስቶቭ ድጋፍ ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡
ከተቋሞቹ የተደረገውን ድጋፍ ምክትል ታከለ ኡማ ከንቲባ ;
በምክትል ማእረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ እንዳወቅ አብጤ እና የአዲስ አበባ የብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በጋራ በመሆን መቀበላቸው ነው የተገለፀው።

ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተቋማቱ ባደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው በተለይ የትምህርት ሚኒስቴር ያደረገው ዘመናዊ ኢንዱስትሪያል ስቶቭ ለትምህርት ቤቶች የምገባ መርሃግብር በእጅጉ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የግብርና ሚኒስቴርም ከዚህ ድጋፍ በተጨማሪ አስተዳደሩ በቅርቡ ተግባራዊ ላደረገው የከተማ ግብርና ዘርፍ አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ላይ መሆኑን ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡ ምንጭ፡-ከንቲባ ፅ/ቤት